አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም
Choose an available translation of this Hadeeth
Hadeeth text
ከሠውባን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ ሶስት ጊዜ ኢስቲግፋር ያደርጉ (ምህረት ይጠይቁ) ነበር። እንዲህም ይሉ ነበር: 'አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም' ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) ወሊድ ለአውዛዒይ 'እንዴት ነው ኢስቲግፋር የሚደረገው? አልኩት' አለ። እሳቸውም 'አሰተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ' በማለት ነው ብለው መለሱልኝ።' አለ።"
Explanation
ቀጥለውም ጌታቸውን "አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም" (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) በማለት ጌታቸውን ያልቃሉ። አላህ በባህሪያቶቹ የተሟላና ሰላም ነው፤ ከሁሉም ጉድለትና ነውርም የጠራ ነው። ከዱንያና አኺራ ክፋት ሰላም የሚፈለገውም ከሌላ ሳይሆን ከርሱ ነው። እርሱ ጥራት ይገባውና በሁለቱም ዓለም መልካሙ የበዛ ፣ የልቅናና መልካም ባለቤት ነው።
Benefits
አምልኮ ውስጥ የጎደለውን እንዲሞላ፣ አምልኮ ውስጥ ያሳነስነውን እንዲጠግን ኢስቲግፋር እንደሚወደድ እንረዳለን።
Attribution
Categories
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares

