HadeethEnc · 1.23.0
ለአቅመ አዳም በደረሰ ሰው ላይ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠብ፣ ጥርሱን ሊፍቅና ካገኘም ሽቶ መቀባቱ ግዴታ ነው።
Available translations
Choose an available translation of this Hadeeth
01
Hadeeth text
ከዐምር ቢን ሱለይም አልአንሷሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "አቡ ሰዒድ እንዲህ እንዳለ እመሰክራለሁ: 'የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ እንዳሉ እመሰክራለሁ: "ለአቅመ አዳም በደረሰ ሰው ላይ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠብ፣ ጥርሱን ሊፍቅና ካገኘም ሽቶ መቀባቱ ግዴታ ነው።"
02
Explanation
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሙስሊሞች መካከል ጁሙዓ ሊሰግድ ግዴታ የሆነበት የደረሰ ወንድ ልጅ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠቡ ልክ እንደ ግዴታ አፅንኦት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገለፁ። በመፋቂያና በመሳሰሉት ጥርሱን ማፅዳቱም፤ እንዲሁም ማንኛውም መልካም መዓዛ ያለውን ሽቶ መቀባቱንም አፅንኦት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገለፁ።
03
Benefits
በሁሉም የደረሰ ሙስሊም ወንድ ላይ የጁሙዓ ቀን መታጠብ እጅግ የሚወደድ መሆኑ አፅንኦት የተሰጠው ጉዳይ እንደሆነ እንረዳለን።
ለአንድ ሙስሊም ንፅህናና መጥፎ ሽታን ማስወገድ በሸሪዓ የሚፈለግ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
የጁመዓ ቀንን ማላቅና ለርሱ መዘጋጀት እንደሚገባ እንረዳለን።
የጁመዓ ቀን መፋቅ ተወዳጅነት አፅንኦት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
ለጁሙዓ ከመሄድ በፊት ጥሩ መዓዛ ያለው ማንኛውንም ሽቶ መቀባት እንደሚወደድ እንረዳለን።
ሴት ልጅ ለሶላት ወይም ለሌላ ጉዳይ ከቤቷ የወጣች ጊዜ ለርሷ ሽቶ መቀባት ክልክል መሆኑን የሚጠቁም ሐዲሥ ስላለ አይፈቀድላትም።
ሐዲሱ ላይ "ሙሕተሊም" በማለት የተፈለገው አቅመ አዳም የደረሰ ማለት ነው። አቅመ አዳምነት በተለያዩ ምልክቶች ይታወቃል። ሶስቱን ወንዶችም ሴቶችም የሚጋሩት ነው። እነርሱም: አንደኛ: አስራ አምስት አመት መሙላት፤ ሁለተኛ: ሸካራ ፀጉር ብልት ዙሪያ የበቀለ ጊዜ፤ ሶስተኛ: በህልም ወይም ከህልም ውጪ እንኳ ቢሆን በስሜት የዘር ፈሳሽ ማፍሰስ ነው። አራተኛው ምልክት ሴቶች ላይ ብቻ የተገደበ ነው። እርሱም: የወር አበባ ነው። ሴት ልጅ የወር አበባ ከፈሰሳት ጊዜ ለአቅመ ሄዋን ደርሳለች ማለት ነው።

Attribution
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
Categories
Share
Share hadeeth
Sharing options · 0 Total shares