الغاشية

 

Al-Ghashiyah

 

The Overwhelming

1 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 001

هَلۡ أَتَىٰكَ حَدِيثُ ٱلۡغَٰشِيَةِ
የሸፋኝቱ (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን?

2 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 002

وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٍ خَٰشِعَةٌ
ፊቶች በዚያ ቀን ተዋራጆች ናቸው፡፡

3 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 003

عَامِلَةٞ نَّاصِبَةٞ
ሠሪዎች ለፊዎች ናቸው፡፡

4 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 004

تَصۡلَىٰ نَارًا حَامِيَةٗ
ተኳሳን እሳት ይገባሉ፡፡

5 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 005

تُسۡقَىٰ مِنۡ عَيۡنٍ ءَانِيَةٖ
በጣም ከፈላች ምንጭ ይጋታሉ፡፡

6 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 006

لَّيۡسَ لَهُمۡ طَعَامٌ إِلَّا مِن ضَرِيعٖ
ለእነርሱ ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃም) ዛፍ እንጅ ሌላ ምግብ የላቸውም፡፡

7 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 007

لَّا يُسۡمِنُ وَلَا يُغۡنِي مِن جُوعٖ
የማያሰባ ከረኃብም የማያብቃቃ ከኾነው፡፡

8 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 008

وُجُوهٞ يَوۡمَئِذٖ نَّاعِمَةٞ
ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው፡፡

9 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 009

لِّسَعۡيِهَا رَاضِيَةٞ
ለሥራቸው ተደሳቾች ናቸው፡፡

10 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 010

فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٖ
በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው፡፡

11 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 011

لَّا تَسۡمَعُ فِيهَا لَٰغِيَةٗ
በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም፡፡

12 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 012

فِيهَا عَيۡنٞ جَارِيَةٞ
በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አልሉ፡፡

13 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 013

فِيهَا سُرُرٞ مَّرۡفُوعَةٞ
በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አልሉ፡፡

14 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 014

وَأَكۡوَابٞ مَّوۡضُوعَةٞ
በተርታ የተኖሩ ብርጭቆዎችም፡፡

15 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 015

وَنَمَارِقُ مَصۡفُوفَةٞ
የተደረደሩ መከዳዎችም፡፡

16 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 016

وَزَرَابِيُّ مَبۡثُوثَةٌ
የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አልሉ)፡፡

17 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 017

أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى ٱلۡإِبِلِ كَيۡفَ خُلِقَتۡ
(ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!

18 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 018

وَإِلَى ٱلسَّمَآءِ كَيۡفَ رُفِعَتۡ
ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች!

19 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 019

وَإِلَى ٱلۡجِبَالِ كَيۡفَ نُصِبَتۡ
ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!

20 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 020

وَإِلَى ٱلۡأَرۡضِ كَيۡفَ سُطِحَتۡ
ወደ ምድርም እንዴ እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?)

21 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 021

فَذَكِّرۡ إِنَّمَآ أَنتَ مُذَكِّرٞ
አስታውስም፤ አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና፡፡

22 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 022

لَّسۡتَ عَلَيۡهِم بِمُصَيۡطِرٍ
በእነርሱ ላይ ተሿሚ (አስገዳጅ) አይደለህም፡፡

23 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 023

إِلَّا مَن تَوَلَّىٰ وَكَفَرَ
ግን (ከእውነት) የዞረና የካደ ሰው፤

24 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 024

فَيُعَذِّبُهُ ٱللَّهُ ٱلۡعَذَابَ ٱلۡأَكۡبَرَ
አላህ ታላቁን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡

25 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 025

إِنَّ إِلَيۡنَآ إِيَابَهُمۡ
መመለሻቸው ወደእኛ ብቻ ነው፡፡

26 - Al-Ghashiyah (The Overwhelming) - 026

ثُمَّ إِنَّ عَلَيۡنَا حِسَابَهُم
ከዚያም ምርመራቸው በእኛ ላይ ብቻ ነው፡፡

Scroll to Top