الفاتحة

 

Al-Fatihah

 

The Opener

1 - Al-Fatihah (The Opener) - 001

بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡{1}
{1} የመክፈቻይቱ ምእራፍ የቁርኣን በላጭ ሱራ ነች። ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ. ለአቢ ሰዒድ እንዲህ አሉ፡- “ከቁርኣን ሱራዎች ውስጥ በላጩን አሳውቅሃለሁ እርሱም አልሃምዱ ሊላሂ ረቢል ዓላሚን- ነው።" {ቡኻሪ ዘግበውታል}።

2 - Al-Fatihah (The Opener) - 002

ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤

3 - Al-Fatihah (The Opener) - 003

ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ

4 - Al-Fatihah (The Opener) - 004

مَٰلِكِ يَوۡمِ ٱلدِّينِ
የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡

5 - Al-Fatihah (The Opener) - 005

إِيَّاكَ نَعۡبُدُ وَإِيَّاكَ نَسۡتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡

6 - Al-Fatihah (The Opener) - 006

ٱهۡدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلۡمُسۡتَقِيمَ
ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡

7 - Al-Fatihah (The Opener) - 007

صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنۡعَمۡتَ عَلَيۡهِمۡ غَيۡرِ ٱلۡمَغۡضُوبِ عَلَيۡهِمۡ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ
የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡ {1}
{1} ኣሚን የምትል ቃል በሶላት ውስጥ እዚህ ትባላለች፤ እንደውም ድምጽ ከፍ በምደረግበት ሶላት ውስጥ ጀማኣው በአንድነት ድምጽ ከፍ ተደርጎ ማለት ያስፈልጋል። ግን እሷ ከፋትሃ አይደለችም።

Scroll to Top